Awesome
ይቅርታ! እኔ በግሌ ከሀናም ከአንቺም ጋር ትውውቅም ሆነ ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም፡፡ ይህንንም እግዚአብሔር ያውቃል፡፡ ተስማምታችሁ ብትሠሩ ከገዳማችሁም ክብርና ደስታ ነበራችሁ፡፡ ነገር ግን ይህ ስላልሆነ ብቻ እኔ አንቺ እንዳትከፊ ብየ ነው የጻፍኩልሽ፡፡ ጥሩ መልስ ትመልሺልኛለሽ ብየ ጠብቄ ነበር፡፡ ለምን እንደተበሳጨሽ አልገባኝም፡፡ እኔ በበኩሌ ለአንቺ በመጻፌ ደስተኛ ነኝ፡፡ ከሀና ጋር የጨረስኩት ነገር ቢሆን ኖሮ ለአንቺ መን ያስጽፈኝ ነበር፡፡ እናም ማድረግ ያለብኝን አስቤ እንዳትከፊ ብየ አድርጌያለሁ፡፡ አንቺም ብዙ የደከምሽ የወንቅ እሸት ልጅ ነሽ፡፡ እሷም ባትግባቡ እንጅ እህትሽ ናት፡፡ ቢሆን ኖሮ እናንተ እህቴ እህቴ ተባብላችሁ ሌላውን ታስታርቁ ነበር እንጅ አትጣሉም ነበር፡፡ ያ ካልሆነ ደግሞ እኛ መፍትሔ ብለን ከእነርሱ የመጣውን እንዳለ ሳንቀበል አንቺንም አማክረን ለመሥራት ስንነሳ እንደዚህ መበሳጨቱ አስፈላጊ አልነበረም፡፡ [read more] ባልጽፍ ይሻለኝ ነበር እንዳልል ይቆጨኝ ነበር፡፡ በመጻፌ ደግሞ ስትበሳጪ አዝናለሁ፡፡ በመጨረሻ አንድ ሁላችንም እየነጋነው ያለነውን ነገር ልንገርሽ አባ ዮሐንስን እንወዳለን፤ እንደ እሳቸው ታጋሽ ሆነን ሰዎችን ችለን አብረን መሥራትን ግን እንዘነጋለን፡፡ ጥሩ ያደረግሁ መስሎኝ ነአጥፍቼ ከሆነ ይቅርታ!
በመጨረሻ እኛ ያሰብነው የሀና ወይም የአንቺ የአንዳችሁን ሀሳብ ለመደገፍ የአንዳችሁን ለመንቀፍ አይደለም፡፡ ያለነው ወንቅ እሸት ስለሆነ አእምሯችን ይሄን እንድንሠራ አይፈቅድልንም፡፡ እኛ ያልነው ፈቃደኛ ከሆናችሁ ፔጁን ሙሉ በሙሉ ለገዳሙ አስረክቡና ገዳሙ የአድሚንነቱን ሥራ ይሥራ እናንተ ሁላችሁም እንደሚመቻችሁ ክፍት ይሁንላችሁና እየተነጋገርን ጻፉበት ነው፡፡
እሺ አንቺ አሁን የፈለግሽውን መጻፍ ትችያለሽ፡፡ ቁጥጥሩን ወደ እኛ አዙሬዋለሁኝ፡፡ ለሀናም እንዲሁ አደርጋለሁ፡፡ የአንቺ ፌስቡክ አካውንት ማለትም ተስፋ ነሽ የሚለውና ገብርኤል አባቴ የሚለው ምኑም አልተነካም፡፡ ገብተሽ እይውነ ችግር ካለው ንገሪኝ፡፡
እንደ እሱ አይባልም፡፡ እያንዳንዳችን እራሳችንን ለሰዎች እንደሚፈልጉት ካላደረግንላቸው በስተቀር ከማንኛውም ሰው ጋር አብረን መኖር አንችልም፡፡ ደግሞ የፈለገውን የጽድቅ ሥራ ብንሠራ እየተጣላን አባታችንም እግዚአብሔርም አይደሰትም፡፡ እኛ መሆን ያለብን የቀረው ነገር ይቅር እንጅ ጠብ በመካከላችን እንዳይፈጠር ነው፡፡
ገዳማችን አብረን እንድናለግል ከእሷ ጋርም የሻከረውን ልብሽን አስተካክይው፡፡ መቼ ረግጠነው የምምሉትን ገዳም በስደት ሁናችሁ በመጣላት እንዳታሳዝኑት ለእሷም ካገኘኋት እነግራታለሁ፡፡ እባካችሁ እንደ ቀድሞው ለመሆን ሞክሩ፡፡ [/read]
- Go to the previous page
- 1
- …
- 113
- 114
- 115
- 116